=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ሥራ ፈቶች ማለት የብዥታ እና የአሉቧልታ ጡሩምባ ነፊዎች የሆኑት ናቸው። ህሊናቸው እዚህም እዚያ ተበታትኗልና።
አል-ቁርአን 9:87
«በቤት ከሚቀሩት ጋር መሆንን ወደዱ።»
ሰው ስራፈት ሲሆን ህሊናው አደጋ ውስጥ ይሆናል። ሾፌር ሳይኖረው ከዳገት ላይ በፍጥነት እንደሚንደረደር መኪናም ነው። አንዳንዴ ወደ ቀኝ አንዳንዴም ወደ ግራ ይወዛወዛል።
በህይወትህ ውስጥ ስራ ፈት ስትሆን ለጭንቀትና ለትካዜ እንዲሁም ለድንጋጤ ዝግጁ ትሆናለህ። ምክኒያቱም ስራ ፈት ስትሆን የትናንት ፣ የዛሬንና የነገን መዝገቦች በሙሉ ፊት ለፊትህ ትደቅናቸውና በተምታታ ነገር ውስጥ ይጥሉሃል። ስለዚህ ራሴንና አንተንም የምመክረው ነገር ቢኖር ገዳይ ከሆነው ስራ ፈትነት መላቀቅ እና ፍሬያማ ተግባራትን ማከናወን እንዳለብን ነው። ምክኒያቱም ስራ መፍታት ድብቅ የሆነ ራስን ከነ ህይወት የመቅበር ዘዴ እና ቀስ እያሉ እራስን እንደማጥፋት ነው።
ስራ መፍታት ምሳሌው በቻይና አገር እስረኞችን ለማሰቃየት እንደሚጠቀሙት የቧንቧ ውሃ ጠብታ ነው። እስረኛውን አስቀምጠውት ጠብታዎቹን እየተጠባበቀ ለእብደት እንዲጋለጥ ይደረጋል።
ረጅም እረፍት ዝንጋቴን ያስከትላል ፤ ስራፈትነትም የተካነ ሌባ ነው ፤ አዕምሮህም በነዚህ ምናባዊ ጦሮች አማካኝነት እንደተበጣጠሰ ግዳይ ነው።
ስለዚህ አሁኑኑ ተነስ ስገድ ፣ ቅራ ፣ አሏህን አወድስ ፣ አንብብ ፣ ፃፍ ፣ የንባብ ቦታህን አስተካክል ፣ ቤትህን አሰነዳዳ ሌሎችን ጥቀም ስራፈትነትን ትገድለው ዘንድ ይረዳሃልና። ላንተ ብዬ ነውና ምክሬን ተቀበለኝ።
ስራፈትነትን በስራ ቢለዋ እረደው። ይህንን በማድረግህ ብቻ የዓለም ሃኪሞች ደስታን 50% ዋስትና ይገቡልሃል። አቡኪዎችን ፣ ገበሬዎችንና ግንበኞችን ተመልከታቸው እንደ ወፍ ይዘምራሉ። ተደስተዋል ፣ አርፈዋልም አንተ ግን ፍራሽህ ላይ ሆነህ እንባህን ታብሳለህ ፤ ተነደፍኩም ብለህ ትጨነቃለህ።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|